ወላጆች እና ልጆች - ቋንቋ

ልጅን በራስ ቋንቋ ማነጋገር ብዙ ጥቅሞች አሉት
አንድ ልጅ በፍጥነት አፍ እንዲፈታ ከተፈለገ ምርጡ መንገድ በተቻለ መጠን እንደልብ በሚናገሩት በራስ ቋንቋ ልጁን ማነጋገር ነው።
የአፍ መፍቻዎ ባልሆነ ቋንቋ ሐሳብዎን፣ ፍቅርዎን፣ ሥጋትዎን፣ በአጠቃላይ ውስጣዊ ስሜትዎን እንደሚፈልጉት በማይገልጽልዎ ቋንቋ አንድ ሕጻንን ማናገር፣ የልጅዎን ሰብዓዊ ባሕርይ ካለማጐልበት በተጨማሪ ከእርስዎ ባሕርይ ጋር የሚያገናኘውን ድልድይ አለመገንባትን ሊያስከትል ይችላል። በእስራኤል አገር የሚያድጉ ሕጻናት የዕብራይስጥ ቋንቋ ችሎታቸው የመጠቀ የሚሆንበት ዕድል የተመቻቸ ነው። ሕጻናት ቋንቋውን በላቀ ሁኔታ ከአነጋገሩ እስከ አገባቡ ሥርዓት ባለው መንገድ በት/ቤት ውስጥ መማር ይችላሉ። እንደዚሁም ከሰፈር ልጆችና በተለያዩ ቦታዎች ቋንቋቸውን ማዳበር ይችላሉ። እንደዚያ ከሆነ ሕጻናት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን የመማር ዕድል የላቸውም ማለት ነው። ስለሆነም የአፍ መፍቻ ቋንቋዎ ካልሆነ ልጅዎን በግድ በዕብራይስጥ ማናገር የለብዎትም። በራስዎ ቋንቋ ማለትም በአማርኛ ወይም በትግርኛ ሆነ በሌላ የአፍ መፍቻዎ ቋንቋ ካነጋገሩት ልጅዎ በአስተማማኝ ሁኔታ አፍ ይፈታና ትምህርት ሲጀምር ወይም መዋዕለ ሕጻናት ሲገባ የዕብራይስጥ ቋንቋን ለመናገር አዕምሮው ዝግጁ ይሆናል። አንዳንድ ቤተሰሰቦች ከተሞክሮአቸው እንደሚመሰክሩት ወላጆች ሙሉ ሐሳባቸውን ያለገደብ በሚገልጹበት በራሳቸው ቋንቋ ልጆቻቸውን ቢያናግሩ፤ ከልጆቻቸው ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት ከመፍጠር ባሻገር፤ በልጆቻቸው ላይ ፈጣን የአዕምሮ ዕድገትን በማምጣት ጥሩ የትምህርት ውጤትን እያስገኙ ነው። ልጅዎ የአፍ መፍቻ ቋንቋውን ቢችል እንዲናገር ባይችል እንኳን መሠረታዊ የቋንቋው ዕውቀት በጭንቅላቱ እንዲቀረጽ እንዴት እንደሚያስችሉት “ናሽናል ሊትረሲ ትረስት” (National Literacy Trust) ከተሰኘው ከእንግሊዙ የትምህርት በጐ አድራጐት የተገኙ ጠቃሚ ምክሮች ከዚህ በታች ቀርበዋል። (1) ልጅዎን ሲያጥቡ፣ ሲመግቡ ወይንም ልብስ ሲቀይሩ ባይገባውም እንኳን ምን እያደረጉ እንደሆነ ያጫውቱት። ምክንያቱም ከአንደበትዎ የሚወጣው ድምጽ ወይም ዜማ በልጅዎ አዕምሮ መመዝገብ ይጀምራልና። (2) በቋንቋዎ ተረት፣ ግጥም እና ዜማዎችን እያነበቡ እና እያዜሙ ከልጅዎ ጋር
ይጫወቱ። በተለይም ገላውን በሚያጥቡበት ጊዜ በቋንቋዎ ያዚሙለት። (3) ከመኝታ በፊት ልጅዎን በራስዎ ቋንቋ ተረት እየተረቱለት የትረካው ተካፋይ እንዲሆን ይገፋፉት። (4) ለልጅዎ ከቻሉ በራስዎ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ይፈልጉለት። ካልተቻለዎትም ራስዎ ለመፍጠር ይሞክሩ። የተረትዎን መልዕክት ሕጻኑ ለጊዜው ላይረዳው ቢችልም በአዕምሮው ስለሚቀረጽ ለወደፊት የቋንቋው ክህሎት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። (5) ልጅዎን ከሌሎች ተመሳሳይ ቋንቋ ተናጋሪ ቢጤዎቹ ጋር እንዲጫወት ይገፋፉት።
(6) በልጅዎ የቋንቋ አጣጣል እና ስሕተት አያሹፉ ወይም አይሳቁ። (7) ልጅዎ በመዋዕለ ሕጻናትም ይሁን በመጫወቻ ቦታዎች ስላሳለፈው ውሎው በራስዎ ቋንቋ ያነጋግሩት። በጨዋታችሁ መሐል ዕብራይስጥ ቋንቋን ከተጠቀመ የተናገረውን በራስዎ ቋንቋ ይድገሙለት። (8) ወደ ገበያ ወይም ሱፐርማርኬት በመሄድ የተለያዩ ነገሮችን እየገዙ ከሆነ ምን እየገዙ እንደሆነና ለምን እንደሚገዙ ለሕጻንዎ ያጫውቱት። (9) ልጅዎ በራሱ ቋንቋ እንዲኰራ ያግዙት። ማሳሳቢያ፡- ይህ ጽሑፍ የቀረበው ልጅ/ሕጻን እየተባለ በተባእታይ ጾታ ቢሆንም ሴት ልጆችንም ሆነ ሕጻናትን እኩል ይመለከታል።

חדש!

פרק ראשון - האלפבית - ግእዝ

  המספר הכולל של אלפבית בגעז הוא שלושים, עשרים ושש סטנדרטיים וארבע כלאיים מהשפה האמהרית.     עברית ግ...

פאב אלמז

קטגוריות מובילות

מתח רומן פילסופי ילדים מדע היסטוריה

טופס יצירת קשר

שם

אימייל *

הודעה *