ምጽዓተ ማዐበል - ከጌቱ ሀይሉ

ዐባክህ ዓምላኬ ዝናቡን ዓውርደው
ተሰነጣጠቀ ደረቀብኝ ማሳው ፥
ይለምናል ጌታን ምስኪኑ ገበሬው፤
ለከብቶቼ ግጦሽ ለልጆቼ ቆሎ፤
ለግብር መክፈያ ማሽላ በቆሎ፤
ፍጠን ድረስልኝ ዝናቡ ና ቶሎ ፥
ኤጭ ይሄ ዝናብ ተመልሶ መጣ፤
ዓርፌ ልቀመጥ ደጅም ዓያስወጣ፤
ጭቃ ብቻ ሆነ ዓያስኬድ መኪና፤
ይህ ዓሮጌ ሰፈር ያልረባ ጎዳና፤
ይላል ባለቪላው በረዳው ላይ ሆኖ
ዓፍንጫውን ሳይቀር በጋቢ ጀቡኖ
የዘንድሮው ዝናብ መነቸከ ባሰ፤
ጣራው ዓረግርጎ ግድግዳው ፈረሰ፥
ዐባክህ ዝናቡ ተው ውረድ በቅጡ፤
ዓትጨክን በድሃ ዓትሁንብን ቁጡ፤
ትላለች በብሶት ጠላ ሻጭዋ ደሃ፤
ድስት ዐየደቀነች ለፍሳሹ ውሃ፥
ዝናብም ልመና ይሰማል በቶሎ፤
ይመጣል በርዶ ነፋስን ቀላቅሎ፤
ነጎድጓድም ሳይቀርመብረቅ ዓስከትሎ፤
በደረቁ ምድር ዓጉረምርሞ ዓለፈ፤
ባረባው ጎዳና ሸክሙን ዓሳረፈ፤
ግድግዳ ዓፈረሰ ጣራውን ነቀለ፤
ለፈለገው ትቶ ላልፈለገው ጣለ፤ 
ሠፍራ መለየጽ በቀልቡ የታለ፤
ይህንን የሰማ ያየ ያስተዋለ፤
ጩኸት ዓስተጋባ ዐሮሮው ቀጠለ፤
ዓይ ዝናብ ዓይ ዝናብ ያንተ ሠራ ዐያለ _ _ _
ደራሲም ተነሳ ብዐሩን ዓሾለ፤
መከተቡን ያዘ ወረቀት ቆለለ፤
 ርዐሱን ሲሰይም ማዐበል ነው ዓለ።

חדש!

פרק ראשון - האלפבית - ግእዝ

  המספר הכולל של אלפבית בגעז הוא שלושים, עשרים ושש סטנדרטיים וארבע כלאיים מהשפה האמהרית.     עברית ግ...

פאב אלמז

קטגוריות מובילות

מתח רומן פילסופי ילדים מדע היסטוריה

טופס יצירת קשר

שם

אימייל *

הודעה *